የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ክላስተር አደረጃጀትና የቢሮዎች ሽንሸና ውጤት።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ ከተማ ወላይታ ሶዶ ሆናለች።

👉 ክላስተር 1 ወላይታ ሶዶ:-
በከተማ መመዘኛና ውጤት አሰጣጥና አወሳሰን መመሪያ መሠረት 92% በማስመዝገብና በፖለቲካ ውሳኔ 85% የካቢኔ ድጋፍ በማግኘት።
1. ርዕሰ መስተዳደር ቢሮ
2. ም/ር/መስተዳድር ጽ/ቤት
3. ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት
4. ሰላምና ፀጥታ ቢሮ
5. ጤና ቢሮ
6. ፕላን ቢሮ
7. ፋይናንስ ቢሮ
8.ዋና ኦዲተር ቢሮ
9. ገቢዎች ቢሮ
10. ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ቢሮ
11. ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ቢሮ
12. ፐብሊክ ሰርቪስ ኮሚሽን ቢሮ
13. ከላይ የተጠቀሱ ቢሮዎች ተጠሪ ተቋማት

👉 ክላስተር 2 ጋሞ ዞን አርባምንጭ:-
በከተማ መመዘኛና ውጤት አሰጣጥና አወሳሰን መመሪያ መሠረት 85.6 % በማስመዝገብና በፖለቲካ ውሳኔ 15% የካቢኔ ድጋፍ በማግኘት።
1. የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት
2. ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ
3. ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ
4. ኢንተርፕራይዝ ስራ ዕድል ፈጠራ ቢሮ
5. ኢንዳስትሪ ቢሮ
6. ብዙሃን መገናኛ ቢሮ
7. ባህልና ቱሪዝም ቢሮ
8. ከላይ የተጠቀሱ ቢሮዎች ተጠሪ ተቋማት

👉 ክላስተር 3 ጌዲዮ ዞን ዲላ:-
በከተማ መመዘኛና ውጤት አሰጣጥና አወሳሰን መመሪያ መሠረት 87% በማስመዝገብና በፖለቲካ ውሳኔ 15 % የካቢኔ ድጋፍ በማግኘት።
1. ግብርና ቢሮ
2. ውሃ ማዕድን ኢነርጂ ቢሮ
3. አካባቢ ጥበቃ ቢሮ
4. ትራንስፖርትና መንገድ ቢሮ
5. ከላይ የተጠቀሱ ቢሮዎች ተጠሪ ተቋማት

👉 ክላስተር 4 ደቡብ ኦሞ ዞን ጂንካ:-
በከተማ መመዘኛና ውጤት አሰጣጥና አወሳሰን መመሪያ መሠረት 59.7 % በማስመዝገብና በፖለቲካ ውሳኔ 5% የካቢኔ ድጋፍ በማግኘት።
1. ትምህርት ቢሮ
2. ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
3. ሰራተኛና ማህበራዊ ቢሮ
4. አርብቶ አደር ጉዳዮች ቢሮ
5. ቴ/ሙ/ት/ስ ቢሮ
6. ከላይ የተጠቀሱ ቢሮዎች ተጠሪ ተቋማት

👉 ክላስተር 5 ጎፋ ዞን ሳውላ:-
በከተማ መመዘኛና ውጤት አሰጣጥና አወሳሰን መመሪያ መሠረት 62.6 % በማስመዝገብና በፖለቲካ ውሳኔ 10% የካቢኔ ድጋፍ በማግኘት።
1. ፍትህ ቢሮ
2. ጠቅላይ ፍ/ቤት
3. ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ
4. ማረሚያ ቤቶች ኮሚሸነር ቢሮ
5. ከላይ የተጠቀሱ ቢሮዎች ተጠሪ ተቋማት

👉 ክላስተር 6 ኮንሶ ዞን ካራት:-
በከተማ መመዘኛና ውጤት አሰጣጥና አወሳሰን መመሪያ መሠረት 25.7 % በማስመዝገብና በፖለቲካ ውሳኔ 5% የካቢኔ ድጋፍ በማግኘት።
1. ብሔረሰቦች ም/ቤት
2. ሳይንስና ቴክኖሎጂ ቢሮ
3. ፀረ ሙስናና ስነምግባር ቢሮ
4. ከላይ የተጠቀሱ ቢሮዎች ተጠሪ ተቋማት

ከላይ የተሸነሸኑ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቢሮዎች የ6 ዞኖችና 5 ልዩ ወረዳዎች የሕዝብ ተወካዩች በፌዴራል፣ በክልል፣በዞን፣ልዩ ወረዳ ያሉ በተካተቱበት ግልፅና ፍትሃዊ በሆነ መንገድ አንድ አቋም በመያዝ በይሁንታ የተፈፀመ መሆኑ ሂደቱን ተዓማኒ ያደርገዋል።

በመሆኑ በዜጎች መተማመንና በጎ ፍቃድ በውይይት ላይ የተመሰረተ የውሳኔ ሀሳብ ስለሆነ ሁሉም ሀገር ወዳድ ዜጋ የመንግስትን አቅጣጫ ወደ መሬት በማውረድ ለሀገር ብልፅግና እጅ ለእጅ በመያያዝ ወደ ስራ መገባት እንዳለበት ተጠቁሟል።

የምስረታ ሂደት፣መቼት፣የአመራር ምደባ፣የሃብት ክፍፍል በቀጣይ ዘገባችን በሰፊው እንመለስበታለን።
From Excellency center by Fb