DireTube
DireTube @diretube

Smile!

DireTube
DireTube @diretube

የመረጃና ደኅንነት አገልግሎት እና የብሔራዊ ባንክ ህገወጥ የውጭ ምንዛሪና የገንዘብ ዝውውር ተዋናዮችን በጥናት በመለየት ቀጣይ እርምጃ እንደሚወሰዱ አስታወቁ።

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት በህገወጥ የገንዘብ ዝውውርና ህገወጥ የውጭ ምንዛሪ እንቅስቃሴ ዙሪያ ያካሄደው ሰፋ ያለ ጥናት ዛሬ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ይፋ ሆኗል።

አገልግሎት መሥሪያ ቤቱ ለመገናኛ ብዙኃን በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ የብሔራዊ ባንክ ገዢ ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት፣ የተለያዩ የመንግስት ተቋማት የሥራ ሃላፊዎች፣ ኮሚሽነሮች እንዲሁም የደኅንነት እና የፀጥታ ተቋማት ኃላፊዎችና ባለድርሻ አካላት በተሳተፉበት የውይይት መድረክ የቀረበው ጥናት በዘርፉ ያሉትን ችግሮች እንዲሁም የተለያዩ የውጭ ሀገራትን ተሞክሮም ጭምር በጥልቀት የዳሰሳ ነበር።

ጥናቱን ግኝቶች መነሻ በማድረግ ህገወጥ የውጭ ምንዛሬና የገንዘብ ዝውውርን ሰንሰለት ለመበጠስ እንዲሁም የድርጊቱ ተዋናዮች ላይ እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችል የፖሊስ፣ የሥርዓትና የተጠያቂነት መፍትሄዎችን የሚጠቁሙ ምክረ ሐሳቦችን እንዲሁም በቀጣይ ሊወሰዱ የሚገባቸውን ህጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃዎችንም አመላክቷል።