ድንቅ የፍቅር ግጥም

በአፍቅሮተ ራስ ጥማት
ውዴ ትለኛለች ፍቺ እየጠየኳት

#3 - መቆጣጠር የምትችለውን ዕወቅ

አቅምና መሉ ቁጥጥር ያለህ በራስህ አዕምሮ እና ንቃተ ህሊና ላይ እንጂ ካንተ ውጪ ባሉ ክንውኖች ላይ አይደለም፡፡ ይህንን አውቆ መተግበሩ ጥንካሬን ያጎናፅፋል፡፡

አስበው ፈረስ ስትጋልብ ቁጥጥርህ ልጓሙ ላይ እንጂ ፈረሱ ላይ ሊሆን አይችልም ልጓሙን ትተህ ፈረሱን በአካል ልቆጣጠር ካልክ ሂደቱ የጭንቀት ከፍተኛ ጉልበት የማውጣትና የእልህ አስጨራሽ ትግል ..... ውጤቱ ደግሞ አፈርድሜ መብላት ...... እመነኝ ፈረሱን ትተህ ልጓሙን ያዘው አዕምሮህን ማለቴ ነው

#Kerkirgard "ድባቴና ጭንቀት ድምፅ አልባ ገዳዮች እየሆኑ መጥተዋል"

ከድባቴ ፣ ከጭንቀት እና ከነፍስ ተስፋ መቁረጥ ወጥተህ እውነተኛ የማንነት ዕድገት መገንባት ከሆነ ትልምህ መቆጣጠር የማትችለውን አምነህ ተቀብለህ የሀይል ሚዛን ትኩረትህን መቀየር በምትችለው ላይ አድርገው፡፡

የእጅ ሰዓትን አሽከርክሮ አቅጣጫውን ትክክለኛው ቁጥር ላይ አድርጎ የማስጀመር አይነት ..... አሁኑኑ የህይወት መስመርህን አቅጣጫ በትክክለኛው ላይ አድርገህ አጥብቀው .... በቃ ባትሪ እስከምትጨርስ ህይወትህን ቀጥል፡፡

ልዑለሥላሴ ፀጉ

#2 የቂሎች ወርቅ

ከመካከላችን በጣም አንኮሎ ፣ ነሆለል ፣ ዝፍጥ የሆነው ሁሌም ቢሆን ትርጉም ካለውና ከተመረመረ ህይወት ይልቅ ሀብትን ያስበልጣል፡፡

ገንዘብ ጥበብና ንቃትን ሊገዛ አይችልም እናም ያልተፈተሸ የገንዘብ ፣ የስልጣን ፣ የአብረቅራቂ ነገሮች ጥመኝነት ጊዜ ቅል ሲሰጠው እያንዳንዳቸውን ድንጋዮችና የግለሰብ ህይወትን ማውደሙ አይቀርም፡፡

#Epicurus " በጥቂቱ መርካትና በሂደት መደሰት ካልቻልክ የግብህ ውጤት አልቦ(0) ብቻ ነው፡፡"

(እያወራሁ ያለሁት ተራ ዲስኩር ለመሰላችሁ የፅሁፌን መጀመሪያ ድጋሚ አንብቡት ከመካከላችን ..... ይላልና ራሳችሁን ፈትሹ)

ዋነኛ ትኩረትህን ንቃት ፣ መልካም ስብዕና እና ትርጉም ያለው ህይወት መገንባት ላይ አድርገው ....
ገንዘብ ያስፈልጋል? አዎ በሚገባ ነገር ግን ገንዘብ መጠቀሚያ ብቻ ነው እንጂ የመጨረሻ ግብህ ሊሆን አይገባም አይ ካልከኝ ግን ሁሉን ትተህ እጅህን አጣጥፈህ ተቀመጥ ትርጉም የሌለው ህይወት ሩጫ ውጤቱ አልቦ ነውና አልቦ ደግም በምንም ቢባዛ ያው አልቦ ነው፡፡

አስተውል

የትኛውም በአሸዋ ላይ የተገነባ መሰረት ሳይሰነብት ውቅያኖሱን ማየቱ አይቀርም፡፡
ይቀጥላል ....

#1- መዳረሻህን አስፋ(ለጥጠው)

አካባቢን መለወጥ እና ከህልምህ ጋር የሚገናኝ ከባቢን መፍጠር አስተሳሰብን የመለወጥና አንተን ከህልምህ ጋር የመስፋት ጥልቅ አቅም አለው፡፡

ሯጭ የመሆን ህልም ሰንቀህ የምትውለው የባልትና ውጤቶች የሚዘጋጁበት ቦታ ከሆነ እመነኝ ከእግርህ ይልቅ ፈጣን የሚሆነው እጅህ ነው(በርበሬ ቅንጠሳ ላይ ማለቴ ነው)፡፡

#Seneca ይለናል "ሰማይ ላይ ደምቀው የሚያበሩትን ኮከቦች ተመልከታቸው አንዳቸውም ተመሳሳይ ቦታ ላይ አይቆዩም"

ጥበብና የማንነት ዕድገትህን መሻትህ ከልብህ ከሆነ የምቾት ቀጠናህ ላይ ማዝገምህን ይብቃህ በለው፡፡
ብዙ በተንቀሳቀስክ ቁጥር የምታገኘው እልፍ ነውና፡፡
......... ይቀጥላል