0%
Habte Michael Lema

Habte Michael Lema

Active Entertainment & Technology

💠 ብዙ ልጆች አሉት 💠
፲፪፲፪፲፪፲፪፲፪፲፪፲፪፲፪፲፪

ብዙ ልጆች አሉት ለስሙ ምስክር
በዙሪያው ያሉትን አብቅትዋል ለክብር
ስለ ፍዕም ምልጃው ለኔ ግን ይለያል
መልዓኩ ሚካኤል ስሱው ደስ ይለኛል
💠
ከመላእክት ክብሩ ከፍ ከፍ ብሎ
ባምላክ የተሾመ ዘንዶውንም ጥሎ
አሳዳጊዬ ነው ሙሉ እናት አባቴ
ሚካኤል ባለበት ይሸሻል ጠላቴ
💠
ከሚታየው ሁሉ ልቤ ከሚፈራው
ካላየሁት ነገር ጠላት ከሰወረው
ያድነኛል ፈጥኖ በመንገዴ መጥቶ
ሚካኤል ሀያሉ ክንፎቹን ዘርግቶ
💠
በባህራን ታሪክ በነ ተላፊኖስ
ባፎምያ መትረፍ በነ ዱራታዋስ
በነብዩ ዳንኤል መች ይፈፅምና
የሚካኤል ስራ ይቀጥላል ገና
💠
በጉዞ የረዳችው በባህር በየብሱ
ፈጥኖ ደርሶላችሁ እንባ ስታፈሱ
ስለታችሁ ሰምራዋል ቁሙ ለዝማሬ
በሚካኤል ምልጃ የቆማችሁ ዛሬ
💠
ክብር ለሚገባው ክብር እንሰጣለን
ንጉሥ ለወደደው እንሰግድለታለን
እንኳን ለሚካኤል ለሚቆም ጌታ ፊት
ክብር እንሰጥ የለ ለምድር ሹማምንት

እንኳን ለኃያሉ የእግዚአብሔር መልዓክ መጋቤ ብሉይ ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ መታሰቢያ ክብረ በዓል አደረሳችሁ አደረሰን ። ዛሬ በዋናነት የሚከበረው በዓለ ሲመቱ ሲሆን ቅዳሴ ቤቱ የከበረበት እንዲሁም አፎሚያን የረዳበት እለት ነው ። ምልጃው አይለየን 💠 #ዚምራ_ቲዩብ #Zimra_Tube #selamEthiopia

ቅዱስ ሚካኤል ፦ ጠባቂ መልዕክተኛ ብቻ አይደለም ባህራንን የዳረ ሽማግሌም እንጂ ።

የአፎሚያ ረዳት የባህራን ወዳጅ ታዳጊ ጠባቂያችን ቅዱስ ሚካኤል ኢትዮጰያን ከጥፋት ሕዝቡን ከስደት ይጠብቅልን። #selamEthiopia #zimra_Tube #ዚምራ_ቲዩብ

ገብርኤል መላከ ሰላም መላከ ብሥራት

አማኑኤል- እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሆነ

ሚያዚያ ፳፰ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም

ነቢዩ ኢሳይያስ ‹‹እነሆ ድንግል በድንግልና ትጸንሳለች፤ ወንድ ልጅንም ትወልዳለች፤ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች›› በማለት ትንቢት እንደተናገረው የተስፋው ቃል ይፈጸም ዘንድ በዘመነ ሥጋዌ እግዚአብሔር ወልድ ከንጽሕተ ንጹሐን ከቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነሥቶ እንደሚወለድ መልአኩ እንዲህ ሲል አበሠራት፤ ‹‹እነሆ ትፀንሻለሽ፤ ስሙንም አማኑኤል ትይለዋለች፤ አማኑኤል ማለት እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ማለት ነው።›› (ኢሳ.፯፥፲፬፣ማቴ.፩፥፳፫)

አማኑኤል ‹አማነ› እና ‹ኤል› ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው፤ ትርጓሜውም የአምላክ ሰላም፣ የእግዚአብሔር እርቅ፣ የጌታ አንድነት ማለት ነው። አማኑኤል ማለት እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ማለት ነው። እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ማለት ደግሞ ከሥጋችን ሥጋ ከነፍሳችን ነፍስ ነሥቶ የተዋሐደ ከብቻዋ ከኃጢአት በቀር እንደኛ የሆነ ማለት ነው።

አዳም ዕፀ በለስን በልቶ የሞት ፍርድ በተፈረደበት ጊዜ በምድር በኃዘን ስለኖረና አምላኩ እግዚአብሔርን ለረጅም ዓመታት ስለተማጸነው በርኅራኄው ወደ ቀድሞ ቦታው እንዲመልሰው በሰጠው ተስፋ ከልጅ ልጁ ተወለዶ አዳነው፡፡ በዚያችም በተከበረች ቀን ትንቢቱ ተፍጽሞ አምላካችን ከእኛ ጋር ሆነ፡፡

አምላክ ሰው የሆነለት የሰው ልጅ ኃጢአት ተፍቆ ነበር፡፡ ስለዚህ ከኃጢአት ርቀን በስሙ ተቀድስን እንድኖር የእግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ የሰው ልጅ ሕይወት ይቀደሳል ማለት ነው፡፡ ሰው ደግሞ መልካም ከሆነ ሁል ጊዜ እግዚአብሔር አይለየውም፡፡

ሰዎች በሕይወት ዘመናችን ችግርና መከራ ሲጸናብንና ፈተናችን ሲበዛ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር እንደሆነ ማሰብ ያዳግተናል፤ እንዲያውም ጨርሶ እንደተወንም እናስባለን፡፡ ሆኖም ግን ፈጣሪያችን ሁሉን የሚያደርገው በምክንያት በመሆኑ ፈተናችን ለበጎ እንደሆነ በማሰብ ጸንተን መጓዝ ያስፈልጋል፡፡

በተለይም በዚህ ጊዜ ችግራችን በዝቶ፣ የእርሱ በርሱ ጦርነት ብሶና የኮሮና ወረርሽኙ ተስፋፍቶ ብዙዎችን እየጨረሰ ባለበት ወቅት እኛ ክርስቲያኖች በሃይማኖት ልንጸናና ልንበረታ ይገባል እንጂ ችግራችንን እያገዘፍን አምላካችንን የምናማርር ከሆነ መፍትሔ አናገኝም፡፡ ምክንያቱም እግዚአብሔር ፍጥረቱን በሙሉ የማይረሳ አምላክ ስለሆነ ከሁላችንንም ጋር ይኖራል፡፡ ከእኛ የሚጠበቀው እርሱን የሚያስደስት ሥራ በመሥራት በክርስቲያናዊ ሕይወት ውስጥ በሕገ እግዚአብሔር አምልኮትን በመፈጸም፣ ለአምላካችን በመገዛትና ትእዛዛቱን በመፈጸም በጽናት መኖር ነው፡፡

አምላካችን እግዚአብሔር አይለየን፤ አሜን፡፡🥰